ደራሲ እታለም እሸቴ

Thank you for joining us at our books launch event. Your presence made the day truly special and we appreciate your support on this journey. We hope you enjoy reading our books as much as we enjoyed sharing them with you.

የአራት ረጂም ልብወለድ መጻህፍት ደራሲ ነች:: ከቤተሰብ ጋር ወደ ሆላንድ ሄዳ ሳለች፣ ከ1993 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ 1994 ዓ. ም. ባለው ጊዜ የመጀመሪያ መጽሀፏን ‘’ምንዳ’’ን ጽፋ ጨረሰች:: ይህንን ሥራዋን ግን ወዲያው ለአንባቢያን አላቀረበችም:: ከሆላንድ ወደ እንግሊዝ ሀገር መጥታ፣ ዓመታት ቆይታ በ2001 ዓ. ም. ነው ያሳተመችው:: ሁለተኛ መጽሀፏን “ሕልመኛዋ እናት”ንም በ2004 ዓ. ም. ለአንባቢያን አቅርባለች:: የአዲስ አበባን ውጣ ውረድ፣ ሳቅ ሀዘን፣ የሠፈር ፈረሳ፣ ፍቅር፣ ወዘተ Continue reading

በቅርቡ በሀገር ፍቅር ቴአትር ለአንባቢያን የቀረቡ
የረጅም ልብወለድ እና የግጥም መጻሕፍት ምርቃት በለንደን

ቀንና ሰዓት:Saturday, September 30, 2023, from 2.00pm
(ቅዳሜ፣ መስከረም 19፣ 2016፣ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ)
አድራሻ: Ethiopian Community in Britain Hall
2A Lithos Road, London NW3 6EF

ለለንደን እና አካባቢው የሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን
እና ወዳጆች የአክብሮት ግብዣ።
ለበለጠ መረጃ:በ 07535217504 ወይም 07415235983 ላይ ይደውሉ።

ከ”የመሐረቡ ምስጢር” ለቅምሻ

ታዋቂው ጸሀፊ እና ገጣሚ ሀማ  ቱማ በዚህ  የእታለም እሸቴ  አራተኛ  የረጂም ልብወለድ መጽሀፍ  ሽፋን ገጽ ላይ  የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል:

“በኢትዮጵያ ሰፍነው የቆዩት ሥርዓቶች በተጠቀሙት ሳንሱር፣ ባስፋፉት ኪነጥበብና አፍላቂነትን ገዳይ ቀኖና የተነሳ ስነጽሁፍ በሀገሪቱ በሚችለው ደረጃ ሊያድግ ሳይችል ቆይቷል። ደርግ በይፋ የሳንሱር ሥርዓትን አቋቁሞ፣ ቁጥጥርና አፈናውን ሲያካሂድ፣ ወያኔም ፖለቲካውን ለተከተሉ መጽሀፍትና ደራሲዎች ሜዳውን ፎገራ ሲያደርግላቸው፣ ላልፈለጋቸው ደግሞ ሁኔታውን አክብዶት ቆይቷል። እታለም በዚሁ ዘመን ብቅ ያለች የልብወለድ ደራሲ ናት። ሊሰጣት የሚገባውን አድናቆትና ዕውቅና ግን ገና አላገኘችም። መድረኩ ዛሬም በስነጽሁፍ ሰዎች ሳይሆን ፖለቲካዊ አቋሞችን በሚያጮሁ “የኪነት ሰዎች” በመያዙ ይሆናል። እታለም በመጀመሪያ በ2001 ዓ. ም. “ምንዳ” የተባለውን፣ በ 2004 ዓ. ም. “ህልመኛዋ እናት”ን፣ ለጥቃ ደግሞ በ 2008 ዓ. ም. “ተፈናቃይ ፍቅር”ን አሳትማ ለአንባቢያን አቅርባለች። እኔ እንደ እታለም የረዥም ልብወለድ ታሪኮችን ጽፌ ማቅረብ አልቻልኩም። እታለም ተራቀቅሁ፣ ከበድኩ፣ ተመጻደቅሁ በማይል ቋንቋ ከሶስት መቶ በላይ ገጾችን የሚያልፍና ከብዙኀኑ ህይወት ጋር የተሳሰረ ትረካን አስለምዳናለች። የተፈናቃዮችን ኑሮም እንኖረው ዘንድ በሚታመኑ ገጸባህርያት አማካኝነት አቅርባልናለች። በልብወለድ ጽህፈት አንዱና ዐብይ የሚሆነው ችግር የገጸባህርያቱ ቃለ-ምልልስ እውነተኛ መምሰል አለመምሰሉ ነው። ሁሉም ሲናገሩ አንድ ከሆኑ፣ የምሁሩም የገበሬውም ቋንቋ አንድ ከሆነ፣ ድርቅ ካለ መጽሀፉ ይሰለቻል። አልመስል ይላል። እታለም ግን ይህን እንቅፋት አልፋው ገጸባህርያቱ የወከሉትን ሆነው፣ የቀን ሠራተኛው ምሩቅ ፈላስፋ ሊሆን ሳይቃጣው እራሱን ሆኖ የሚቀርብ በመሆኑ የእታለም ልብወለዶች ሳይሰለቹ ይነበባሉ። ታሪኩን ይመስላሉ። አንባቢንም ይስባሉ። ይህ ደግሞ ታላቅ ችሎታ ነው። እታለም ከዘመናችን የረዥም ልብወለድ ደራሲዎች አንዷና መነበብም ያለባት ናት እላለሁ።” ሀማ ቱማ

ቀደም ሲል በእታለም የተጻፉ መጻሕፍት